Fana: At a Speed of Life!

ሰሜን ኮሪያ ወታደሮቿ ለግልጽ ጦርነት እንዲዘጋጁ ጥሪ አቀረበች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ከአሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ ጋር ለሚደረግ ግልጽ ጦርነት ወታደሮቻቸው አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ኪም ጆንግ ኡን ጥሪውን ያቀረቡት አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ በኮሪያ ልሳነ ምድር የሚያደርጉትን ወታደራዊ ልምምድ አጠናክረው ለመቀጠል መወሰናቸውን ተከትሎ ነው፡፡

ሀገራቱ በቀጠናው የሚያደርጉት የጋራ ወታደራዊ ልምምድ የሚፈራውን የኒውክሌር ጦርነት እውን ሊያደርገው ይችላል ሲሉም አስጠንቅቀዋል፡፡

ኪም ሐሙስ ምሽት በሰሜን ኮሪያ ምዕራባዊ የባህር ዳርቻ ላይ የመድፍና የሌሎች ጦር መሳሪያዎች ልምምድ ሒደትን መከታተላቸው ተገልጿል፡፡

ልምምዱ በጠላት አየር ማረፊያ ላይ የተሰነዘረ ጥቃት በማስመሰል ከባድ አጸፋዊ ምላሽ መስጠትን ኢላማ ያደረገ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ኪም ወታደሮቻቸው ለእውነተኛ ውጊያ ተዘጋጅተዋል ሲሉ ያሞካሹ ሲሆን ÷ በማንኛውም ጊዜ ለመዋጋት ዝግጁ መሆን እና ከቃላት ይልቅ ለትክክለኛ እርምጃዎች ዝግጁ መሆን እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡

የደቡብ ኮሪያ ጦር ልምምዱ በበርካታ ዙሮች የታጀበና የአጭር ርቀት የሚሳኤል ልምምዶችን እንደሚያካትት መግለጹንም አር ቲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.