Fana: At a Speed of Life!

6ኛው ዙር የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ ወጣቶች ስልጠና ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰላም ሚኒስቴር 6ኛ ዙር የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ ወጣቶች ስልጠና መርሐ ግብርን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በዛሬው ዕለት አስጀምሯል፡፡
መርሐ ግብሩ “በጎነት አብሮነት” በሚል መሪ ቃል በባህር ዳር፣ ጅማ፣ ዋቸሞና ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲዎች ነው የተካሄደው፡፡
በ6ኛው ዙር የስልጠና መርሐ ግብር ከ10 ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እንደሚሳተፉ ሚኒስቴሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የላከው መረጃ ያመላክታል፡፡
የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ ልማት አገልግሎት ፕሮግራም ÷ኢትዮጵያ ያሏትን መልካም እሴቶች፣መርሆዎች፣ የሀገርና የሕዝብ ፍቅር ለወጣቱ ትውልድ ለማስተላለፍ ያለመ ነው ተብሏል፡፡
ይህም የወጣቶችን ምክንያታዊነትን፣ የሕይወት መምራት ክሕሎትን፣ የሥራ ባሕልን፣ መልካም ሥነ ምግባርን በማጎልበት ሀገራዊ አንድነትንና ብሔራዊ መግባባትን በማስረጽ ዘላቂ ሰላም መገንባት እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡
በመላኩ ገድፍ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.