Fana: At a Speed of Life!

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ምርምሮች ለኢኮኖሚ እድገት አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለሀገራዊ ልማትና ኢኮኖሚያዊ እድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ ለመወጣት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር አልሞ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴሩ በኢትዮጵያ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው የኢኮኖሚ ዘርፎችን ለመደገፍና አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ አዳዲስ ምርምሮችን ማድረግ የሚያስችለውን የፖሊሲ፣ ስትራቴጂ፣ አደረጃጀት፣ ተልዕኮ ቀረጻ፣ ትግበራና ነባራዊ ሁኔታ ዳሰሳ ላይ ያተኮረ ጥናት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር አካሂዷል።

ከዩኒቨርሲቲው ጋር በመተባበር በኢኖቬሽንና ምርምር ዘርፍ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ምርምርና የኢኖቬሽን አሰራርና ድጋፍ አተገባበር የሚመራበትን አውድ በመፈተሽ ሰነድ ተዘጋጅቶ የማረጋገጫ አውደ ጥናት መደረጉም ተጠቁሟል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ÷ሚኒስቴሩ ዘርፉን ለመምራት የተሰጡትን ተልዕኮዎች በመወጣት ሀገር ወደ ብልጽግና የምታደርገውን ጉዞ በቴክኖሎጂ ለመደገፍ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ነው ብለዋል፡፡

የዘርፉን ሀገራዊ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች እና የማስፈጸሚያ መመሪያዎችን በማዘጋጀትና የዘርፉን ተልዕኮዎች ከዓለም አቀፍ ተሞክሮ ጋር ተጣጥመው እንዲመሩ የሚያስችሉ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ የማስተባበርና የመደገፍ ስራ እየሰራ መሆኑንም አንስተዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ምርምሮችና ድጋፎች ለኢኮኖሚ እድገትና ልማት ዘላቂ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ በሚያስችል የድጋፍና ቅንጅት ስርዓት ሊመሩና ሊተገበሩ እንደሚገባ መገለጹን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.