Fana: At a Speed of Life!

አምራች ኢንተርፕራይዞችን ለማገዝ የክልሉ መንግሥት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል – ኢ/ር ነጋሽ ዋጌሾ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ም/ ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ በቦንጋ ከተማ የአናስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝር መርሐ ግብሩ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር አለባቸው ንጉሴን ጨምሮ ሌሎች የፈዴራልና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

በቦንጋ ከተማ በአናስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች እየተከናወነ ያለው የስራ እንቅስቃሴ ተስፋ ሰጪ መሆኑን ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ገልጸዋል።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አናስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ለማገዝ የክልሉ መንግሥት ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ጠቅሰዋል።

የግብዓትና ብድር አቅርቦት እንዲሁም የገበያ ትስስር ለኢንተርፕራይዞች ለማመቻቸት በትኩረት እንደሚሰራ መገለጹንም ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢንተርፕራይዞቹ የግብዓትና ብድር አቅርቦት እንዲሁም የገበያ ትስስር ችግር መኖሩን ጠቅሰው÷ የክልሉ መንግስት ተገቢውን ድጋፍና እገዛ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.