Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ ዓመታዊ ጉባኤውን ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ ያካሂዳል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ አቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ ለአፍሪካ አባል አገራት የሚያደርገውን ድጋፍ ለመገምገም ዓመታዊ ጉባኤውን ከነገ መጋቢት አራት ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት በአዲስ አበባ ከተማ ያካሂዳል።

ኤጀንሲው ለአፍሪካ አባል አገራት የሚያደርገውን ድጋፍና የቴክኒካዊ ትብብር አተገባበር ለመገምገምና አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ ጉባኤ በየዓመቱ ያደርጋል።

በመሆኑም የአፍሪካ ሀገራት የዘርፉ ተመራማሪዎችና ብሔራዊ የድጋፍ አስተባባሪዎች በተገኙበት ከመጋቢት 4 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ይደረጋል።

ጉባኤው የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኃይል ከፍተኛ አመራሮች፣ የኢፌዴሪ መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ተመራማሪዎች በተገኙበት ከመጋቢት 4 እስከ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ እንደሚካሄድ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.