Fana: At a Speed of Life!

የፖላንድ ህክምና ቡድን ለ2ኛ ጊዜ ሲያከናውን የነበረውን የነጻ ህክምና አገልግሎት አጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ የፖላንድ ህክምና ቡድን ለሁለተኛ ጊዜ ከየካቲት 17 እስከ 26ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በጥቁር አንበሳ እና በጦር ሃይሎች ስፔሻይዝድ ሆስፒታል ሲያከናውን የነበረውን የነጻ ህክምና አገልግሎት አጠናቅቋል።
 
31 የበጎ ፍቃደኛ የህክምና ባለሙያዎች ያቀፈው ቡድን የነርቭ፣ የአጥንት፣ የኩላሊት፣ የሽንት ፊኛና የሽንት ቧንቧ የቀዶ ህክምና አገልግሎቶችን መስጠቱ ተገልጿል፡፡
 
ከኢትዮጵያውያን የህክምና ባለሙያዎች ጋር በተጠቀሱት የስፔሻሊቲ ዘርፎች ላይ የልምድ ልውውጥ ማድረጉንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
 
የቡድኑ አባላት ለህክምና አገልግሎቱ የዋሉ የህክምና መሳሪያዎችንና ግብዓቶችን በእርዳታ ከፖንላድ ይዟቸው እንደመጡም ጠጠቁሟል፡፡
 
የጤና ሚኒስቴር የህክምና ቡድኑ አባላትና የነጻ ህክምና አገልግሎት ዘመቻው የተሳካ እንዲሆን ላገዙ አካላት ምስጋና አቅርቧል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.