Fana: At a Speed of Life!

ሰሜን ኮሪያ ሁለት ክሩዝ ሚሳኤሎች አስወነጨፈች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ደቡብ ኮሪያ እና አሜሪካ ጥምር ወታደራዊ ልምምድ ሊጀምሩ በተዘጋጁበት ዋዜማ ሰሜን ኮሪያ ሁለት ሚሳኤሎችን ማስወንጨፏ ተሰማ፡፡

ሚሳኤሎቹ የኒውክሌር አረር የመሸከም ዐቅም ያላቸው መሆናቸውን ሬውተርስ በዘገባው አመላክቷል።

ሰሜን ኮሪያ ሚሳኤሎቹን ከባሕር ሰርጓጅ መርከቧ ማስወመንጨፏን የደቡብ ኮሪያውን ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ዋቢ ያደረገው ዘገባ ያመላክታል።

ደቡብ ኮሪያ በበኩሏ “ወታደራዊ ኃይሌ ለማንኛውም ጥቃት አፀፋዊ ምላሽ ለመሥጠት በተጠንቀቅ ላይ ነው” ብላለች፡፡

የደቡብ ኮሪያ የሥለላ ድርጅት ከአሜሪካ አቻው ጋር በጥምረት ባላንጣዋ ሰሜን ኮሪያ ስላስወነጨፈችው ሚሳኤል ዝርዝር ሁኔታ እያጠና መሆኑም ነው የተነገረው።

ደቡብ ኮሪያ እና አሜሪካ ከፈረንጆቹ 2017 ወዲህ ታይቶ የማይታወቅ ነው ያሉትን የ11 ቀናት ጥምር የጦር ኃይል ልምምዳቸውን እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል፡፡

ሀገራቱ ልምምዳቸው የተቀናጀ የመከላከል ዐቅማቸውን እንደሚያጠናክር ከወዲሁ ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.