Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ ዓመታዊ ጉባኤውን በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ ዓመታዊ ጉባኤውን በአዲስ አበባ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል።

በጉባኤው ዓለም አቀፉ አቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ ለአፍሪካ አባል ሀገራት የሚያደርገው ድጋፍ ይገመገማል።

ጉባኤው ከዛሬ ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል።

በጉባኤው የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኃይል ከፍተኛ አመራሮች፣ የኢፌዴሪ መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ተመራማሪዎች ተሳታፊዎች ናቸው።

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ ባደረጉት የመክፈቻ ንገግር ፥ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ ዓመታዊ ጉባኤውን ለመጀመሪያ ጊዜ በማዘጋጀቷ ኩራት ይሰማታል ብለዋል።

ኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ አገልግሎት እና ዘላቂ ልማት መጠቀምን እንደምትደግፍም ተናግረዋል።

በቀጣይ ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ አባል ሀገራት ጋር በዘርፉ ያላትን ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥልም አረጋግጠዋል።

በመላኩ ገድፍ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.