Fana: At a Speed of Life!

በልማታዊ ሴፍቲኔት ከ2 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረግ ተችሏል – የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በልማታዊ ሴፍቲኔት ከ2 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረግ መቻሉን የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

እስካሁን በልማታዊ የሴፍቲኔት ሥራ ፕሮጀክት በተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ ችግሮች ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች መድረስ መቻሉም ተመላክቷል፡፡

የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፋንታ ደጀን ÷ ከ2 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተጋላጭ የሆኑ እና በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ተከስቶ በነበረው ጦርነትና ግጭቶች ከቀዬአቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ ማድረግ መቻሉን አንስተዋል፡፡

ከ2009 ጀምሮ በ11 ከተሞች ተግራባዊ ሲደረግ የቆየው የከተሞች ሴፍቲኔት ፕሮጀክት 1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚጠጉ ዜጎችን ተጠቃሚ አድርጓልም ነው ያሉት፡፡

በቀጣይ በሚከናወኑ 2ተኛ እና 3ተኛ ዙር ልማታዊ የሴፍቲኔት ሥራ ፕሮጀክቶችም ከ640 ሺህ በላይ ዜጎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑም ሚኒስትር ዴኤታው ጠቁመዋል፡፡

የሁለተኛው ምዕራፍ የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔትና ሥራ ፕሮጀክት ÷ በአካባቢ ልማት፣ በቀጥታ ድጋፍ እና በስደተኞችና ተቀባይ ማኅበረሰብ ማዋሃድ ፕሮግራሞች እና በመሳሰሉት ከዓለምአቀፍ አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን ከ640 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ዕቅድ መያዙንም ይፋ አድርገዋል፡፡

በቤዛዊት ከበደ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.