Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ የ17ኛ ሳምንት ቀሪ ጨዋታዎች ለሌላ ተስተካካይ መርሐ ግብር ተዘዋወሩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 በ17ኛ ሳምንት ሊካሄዱ የነበሩ ቀሪ ጨዋታዎች ለሌላ ተሰተካካይ መርሐ ግብር ተዘዋውረዋል።

በፕሪሚየር ሊጉ 2015 በ17ኛ ሳምንት በድሬዳዋ ስታዲየም ቅዳሜ መጋቢት 2 ቀን 2015 ዓ.ም የመጀመሪያ ጨዋታ 10 ሰዓት ሃዋሳ ከተማን ከኢትዮጵያ ቡና ያገናኘ ሲሆን÷ ጨዋታው ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

በመርሐ ግብሩ መሰረት ቀጣይ የሳምንቱ ጨዋታዎችን ለማድረግ ግን በከተማዋ በጣለው ያልተጠበቀ ዝናብ ሜዳው በመበላሸቱና በቀላሉ ሊስተካከል ባለመቻሉ አወዳዳሪው አካል ቀሪ በከተማው የሚካሄዱ የመጨረሻ ጨዋታዎች መሰረዛቸውን አሳውቋል።

በዚህም ውድድሩ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ተቋረጦ በተመረጠ ቦታ መካሄዱ ሲቀጥል ከ18ኛው ሳምንት በኋላ ባለው ወቅት በተስተካካይ መርሐ ግብር የሚካሄዱ መሆኑን ከሊግ ካምፓኒው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.