Fana: At a Speed of Life!

አልጋ ወራሽ ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ የሱልጣንነት ሲመት ተቀበሉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአልጋ ወራሽ ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ የሱልጣንነት በዓለ ሲመት ሥነ- ሥርዓት በአፋር ክልል አሳይታ ከተማ ተካሂዷል።

የቀድሞ የአፋር ሱልጣኔት መሪ ሱልጣን ሃንፍሬ አሊሚራህ ከዓመታት በፊት ሕይወታቸው ማለፉን ተከትሎ ነው ወንድማቸው ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ የሱልጣንነት ሹመታቸውን የተቀበሉት።

በሥነ-ሥርዓቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ እና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

በተጨማሪም የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ የጎረቤት ሀገራት ተወካዮች፣ የሃይማኖት አባቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል፡፡

ሱልጣን አሕመድ አሊሚራህ በአፋር ሱልጣኔት 15ኛው ሱልጣን መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በሳሙኤል ወርቃየሁ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.