Fana: At a Speed of Life!

ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር ለጋራ ጥቅም በቅርበት ለመስራት ምንጊዜም ዝግጁ ናት – የቻይና የአፍሪካ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር ለጋራ ጥቅም በቅርበት ለመስራት ምንጊዜም ዝግጁ ናት ሲሉ የቻይና የአፍሪካ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር ው ፔንግ ተናገሩ፡፡
በቻይና የኢፌዴሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ተፈራ ደርበው የሹመት ደብዳቤያቸውን ቅጂ በቤጂንግ ለቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አቅርበዋል።
አምባሳደር ተፈራ በዚህ ወቅት ከቻይና የአፍሪካ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር ው ፔንግ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸው ወቅትም ለተደረገላቸው አቀባበል እና በሀገራቱ መካከል ላለው መልካም ወዳጅነት ምስጋና አቅርበዋል።
አምባሳደሩ የኢትዮጵያ መንግስት ከቻይና ጋር ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ የማጠናከር ፍላጎት እንዳለው አስረድተዋል።
የቻይና የአፍሪካ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር ው ፔንግ በበኩላቸው፥ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቂን ጋንግ በኢትዮጵያ ያደረጉት ጉብኝት ያለውን ጠቀሜታ በተመለከተ አብራርተዋል፡፡
ለሀገራቱ የጋራ ተጠቃሚነት ከአምባሳደሩ ጋር በቅርበት እንደሚሰሩ ያረጋገጡት ውፔንግ፥ የሀገራቱ መልካም ግንኙነት በአምባሳደሩ የቻይና ቆይታ የበለጠ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
በተመሳሳይ አምባሳደር ተፈራ ከቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ክፍል ዋና ዳይሬክተር ሆንግ ሊ ጋር ውይይት አድርገዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ ከአዲሱ የኢትዮጵያ አምባሳደር ጋር ለሁለቱ እህትማማች ሀገራት የጋራ ጥቅም በቅርበት ለመስራት ምንጊዜም ዝግጁ እንደሆኑ ማረጋገጣቸውን የኤምባሲው መረጃ ያመላክታል።
አምባሳደር ተፈራ ÷ ዋና ዳይሬክተሩ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ለሚያደርጉት ጥረት አድናቆታቸውን ገልጸውላቸዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.