Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በአንዳንድ አካባቢዎች ተቋርጦ የነበረውን የኃይል አቅርቦት ወደነበረበት ለመመለስ እየተሰራ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ በአንዳንድ አካባቢዎች ተቋርጦ የነበረውን የኃይል አቅርቦት ወደነበረበት ለመመለስ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡

ባለፈው ቅዳሜ በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት በ50 የኤሌክትሪክ መጋቢ መስመሮች ላይ በደረሰ ብልሽት በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች አገልግሎቱ መቋረጡን የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የዲስትሪቢዩሽን መቆጣጠሪያ ማዕከል ኃላፊ አቶ ባሳዝነው መኮንን ገልፀዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በአብዛኞቹ መጋቢ መስመሮች ተጠግነው አገልግሎቱ ወደ ነበረበት መመለስሱን የጠቀሱት ኃላፊው÷ ቀሪዎቹን አካባቢዎች በፍጥነት ለማገኛኘት በዲስትሪክቶች በኩል እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

መሰል ችግሮችን ለመቅረፍ የቅድመ ጥገና ስራዎች በሰፊው እየተሰሩ መሆናቸውን ገልፀው÷ በቀጣይ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ያለው የማሰራጫ መስመሮች ማሻሻያ ፕሮጀክት ተጠናቆ ስራ ሲጀምር ችግሩ ሙሉ ለሙሉ እንደሚቀረፍም አመልክተዋል፡፡

በተጨማሪ የዛፎች አለመቆረጥ ለሃይል መቆራረጥ መንስዔ ስለሚሆኑ ህብረተሰቡ የኤሌክትሪክ መስመሮችን የሚነካ ዛፍ በሚኖርበት ወቅት በአካባቢው ለሚገኝ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል በማሳውቅ ሊያስወግድ ይገባል መባሉን ከአገልግሎቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.