Fana: At a Speed of Life!

የዘንድሮው የሐጅ ጉዞ ምዝገባ በ11 የምዝገባ ጣቢያ እንደሚካሄድ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘንድሮው የሐጅ ጉዞ ምዝገባ በ11 የምዝገባ ጣቢያ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ የእስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት አስታወቀ፡፡

የዘንድሮው የሐጅ ጉዞ የሑጃጆችን እንግልት ለመቀነስ የምዝገባ ጣቢያዎች ሑጃጁ በአቅራቢያው በሚገኘው የምዝገባ ጣቢያዎች እንደሚከናወን ነው የተገለጸው፡፡

ላለፉት 10 ዓመታት የሑጃጆች ቁጥር መረጃ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በዚህም መሠረት 11 የምዝገባ ጣቢያዎች የሚከፈቱ ሲሆን÷ እንደ ሁኔታው የምዝገባ ጣቢያዎቹ ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ተመላክቷል፡፡

ከቀናት በኋላ የሚጀመረው የዘንድሮው የሐጅ ጉዞ ምዝገባ ለመመዝገብ ተመዝጋቢው በአካል መገኘት ይኖርበታልም ተብሏል፡፡

በዚሁ መሰረት ÷ የአገልግሎት ጊዜው ለመጠናቀቅ ከስምንት ወራት በላይ ጊዜ የቀረው የጉዞ ሰነድ (ፖስፖርት)፣ አንድ ጉርድ ፎቶ ግራፍ፣ የኮቪድ19 ክትባት ማስረጃ ማቅረባቸው ሲረጋገጥ የአገልግሎት ክፍያ በባንክ እንዲከፍሉ ይደረጋል ነው የተባለው፡፡

በቡድን (በጀምዓ) መጓዝ የሚፈልጉ ሑጃጆች 50 ሰዎች በአንድ ቡድን ሆነው ተደራጅተው መመዝገብ እንደሚችሉም ተገልጿል።

ለትውልደ ኢትዮጵያውያን ሑጃጆች ምዝገባ በጠቅላይ ምክር ቤቱ የምዝገባ ጣቢያ ብቻ ይከናወናል መባሉን ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.