Fana: At a Speed of Life!

የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ከኮሮናቫይረስ አገግመው ከሆስፒታል ወጡ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሆስፒታል ገብተው ህክምና ሲከታተሉ የቆዩት የብሪታንያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን አገግመው መውጣታቸው ተነግሯል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ባሳለፍነው ሳምንት በግል ዶክተራቸው ምክር ሆስፒታል መግባታቸው ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፍተኛ የሰውነት ሙቀትን ጨምሮ የቫይረሱን ምልክት ማሳየታቸውን ተከትሎ ለንደን በሚገኝ ሆስፒታል ከገቡ በኋላም በጽኑ ህሙማን መከታተያ ገብተውም የህክምና ክትትል ሲያደርጉ ቆይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን የጤና ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን ተከትሎም በዛሬው እለት ከሆስፒታል እንዲወጡ መደረጉም ነው የተነገረው።

የጤና ባለሙያዎች ምክርን ተከትሎም ቦሪስ ጆንሰን በአፋጣኝ ወደ ስራቸው የማይመለሱ መሆኑን ቃል አቀባያቸው አስታውቀዋል።

በለንደን ቅዱስ ቶማስ ሆስፒታል በነበራቸው ቆይታ እንክብካቤ ላደረጉላቸው የክህምና ባለሙያዎች በሙሉ ምስጋና ማቅረባቸውንም ገልፀዋል።

ምንጭ፦ reuters.com

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.