Fana: At a Speed of Life!

የመከላከያ ሚኒስቴር በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 220 ሚሊየን ብር ድጋፍ ሰጠ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ሚኒስቴር በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 220 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።

የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጂ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት÷ ሰራዊቱ የህዝብ ልጅ በመሆኑ የሀገርና ህዝብን ሰላምና ደህንነት ከማስጠበቅ በተጨማሪ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ አድርጓል፡፡

ሚኒስቴሩ በኦሮሚያ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች 100 ሚሊየን ብር፣ ለሶማሌ ክልል 50 ሚሊየን ብር፣ ለደቡብ ክልል 40 ሚሊየን ብር እንዲሁም ለአማራ ክልል ዋግኸምራ ዞን 30 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ሰራዊቱ በቀጣይም ለዜጎች ያለውን አለኝታነት በተግባር እያረጋገጠ ይቀጥላልም ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.