Fana: At a Speed of Life!

የቦረና አባገዳዎች በዞኑ ለተከሰተው ድርቅ ከተማ አስተዳደሩ ላሳየው አጋርነት ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቦረና አባገዳዎች በዞኑ ለተከሰተው ድርቅ የአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር ላሳየው አጋርነት እና ድጋፍ በምክር ቤቱ ተገኝተው ምጋናቸውን አቅርበዋል::

አባገዳዎቹ የከተማ አስተዳደሩ በችግራቸው ወቅት ከጎናቸው በመቆም ያደረገው ድጋፍ ለተጎጂዎቹ መድረሱን ገልፀው ለዚህም ምክር ቤቱ የከተማውን አመራር እና መላውን የአዲስ አበባ ነዋሪ አመስግነዋል::

የዞኑን ህዝብ በመወከል የመጡት አባገዳዎች ለምክር ቤት እና ለካቢኔ አባላት የቦረናን ህዝብ የባህል አልባሳት በስጦታ ማበርከታቸውን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለቦርና ድርቅ ተጐጂዎች ከ252 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.