Fana: At a Speed of Life!

ለጅማ ዩኒቨርሲቲ 100 ሚሊየን ብር የሚገመት የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለጅማ ዩኒቨርሲቲ ሕክምና ማዕከል ለአንጀት ካንሰር ቀዶ ሕክምና አገልግሎት የሚውል 100 ሚሊየን ብር የሚገመት የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ።

ድጋፉ የተገኘው ከቤልጂየሙ ጌንት ዩኒቨርሲቲ ዩ ዜድ ሆስፒታል መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የሕክምና ቁሳቁሱ ለአንጀት ካንሰር ቀዶ ጥገና፣ ለፅኑ ሕሙማን መቆጣጠሪያ የሚውሉ መሳሪያዎች እና ሌሎች የሕክምና ቁሳቁስን ያካተተ ነው።

በጅማ ዩኒቨርሲቲ የዘለቄታዊ የትምህርትና ምርምር ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ኮራ ጡሽኔ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት ÷ በቤልጂየሙ ጌንት ዩኒቨርሲቲ ዩ ዜድ ሆስፒታል እና በጅማ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ማዕከል መካከል የሚኖረው የትብብር ሥራ ቀጣይነት ያለው ነው።

በቤልጅየም የጌንት ዩኒቨርሲቲ ዩ ዜድ ሆስፒታል  የሕክምና ልዑካን ቡድን መሪ ፕሮፌሰር ፒት ፓቴን በበኩላቸው ÷ ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ሕክምና ማዕከል ጋር የመስራት ፍላጎታቸው ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የሕክምና አገልግሎት ለማሳደግ በሚደረገው ድጋፍም ዩዜድ ሆስፒታል የድርሻውን እንደሚወጣግ ተናግረዋል ።

በአቤኔዘር ታዬ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.