Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና አሜሪካ በልማት እና የዴሞክራሲ ግንባታ ስራዎች እና መሰል ጉዳዮች ላይ መከሩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና አሜሪካ በልማት እና የዴሞክራሲ ግንባታ ስራዎች እና መሰል ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር ያደረጉትን ውይይት አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው ሚኒስትሮቹ በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን አንስተዋል።

በፕሪቶሪያ እና በናይሮቢ ከተደረሰው የሰላም ስምምነት በኋላ ያሉ የአፈጻጸም ሂደቶች፣ በልማት እና የዴሞክራሲ ግንባታ በሚሰሯቸው ስራዎች እና መሰል ጉዳዮች ላይ ሁለቱ ሃገራት መምከራቸውንም ገልፀዋል።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.