Fana: At a Speed of Life!

55ኛው የተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የፋይናንስ፣ የኢኮኖሚ ልማትና ፕላን ሚኒስትሮች መደበኛ ስብስባ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 6 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 55ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የፋይናንስ፣ የኢኮኖሚ ልማትና ፕላን ሚኒስትሮች መደበኛ ስብስባ በባለሙያዎች ደረጃ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

ስብሰባው “የአፍሪካ መልሶ ማገገም እና ለውጥ በማፋጠን አለመመጣጠንና ተጋላጭነትን መቀነስ” በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

በስብሰባው ላይ የአፍሪካ ሀገራት የፋይናንስ፣ እቅድና የኢኮኖሚ ልማት ባለሙያዎች፣ የኮሚሽኑ አባል ሀገራት ተወካዮች፣ የተመድ ተቋማት ኃላፊዎች፣ የልማት አጋሮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የኮሚሽኑ መደበኛ ስብሰባ የአፍሪካ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ልማት አሁናዊ ሁኔታ እንዲሁም በቀጣናው ትስስር ዙሪያ ያሉ ለውጦችን እንደሚገመግም ተገልጿል።

ስብስባው ሚኒስትሮች አፍሪካውያንን እየፈተነ የሚገኘው ድህነት፣ የኑሮ አለመመጣጠንና ሌሎች ፈተናዎች መፍታትን ትኩረት አድርገው እንዲሰሩ ዳግም ቃላቸውን የሚያድሱበት ነው ተብሏል።

በመደበኛ ስብሰባው ባለሙያዎች ለአምስት ቀናት የሚመክሩ ሲሆን÷ የተወያዩባቸውን የተለያዩ አጀንዳዎች ለሚኒስትሮቹ የሚያቀርቡ ይሆናል።

የሚኒስትሮች ስብሰባው መጋቢት 11 እና 12 ቀን 2015 እንደሚካሄድም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.