Fana: At a Speed of Life!

የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ሲያካሂዱት የነበረው ውይይት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በፓርቲው የስድስት ወር አፈፃፀም ላይ ሲያካሂዱ የነበረውን ውይይት አጠናቀቁ፡፡

በመድረኩ ላይ የፓርቲውን የውስጠ ዴሞክራሲ ባህል በማሳደግ በቀጣይ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ትግል በማድረግ የታዩ ጥንካሬዎችን ይበልጥ በማስፋት እንዲሁም ድክመቶችን አርሞ በመሄድ ረገድ ሰፊ ስራዎች ሊሰሩ እንደሚገባ ተጠቅሷል።

የፓርቲ እና የመንግስት ስራዎችን በአግባቡ መከወን የሚያስችል መዋቅር በማጠናከር ከዋና ፅ/ቤት እስከ ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ድረስ የተሰናሰለ የተግባር አፈፃፀም እንዲኖር ለማስቻል ከፍተኛ ስራዎች ሊሰሩ እንደሚገባም ተመላክቷል፡፡

የብልፅግና ፓርቲን መርሆች፣ ስትራቴጂዎች እና ፖሊሲዎችን ወደ ህብረተሰቡ በተቀናጀ መልኩ በማስረፅ በመደመር እሳቤ የተዋጀ የብልፅግና መንገድ መፍጠር ትልቁ የቤት ስራ እንደሆነ በመገንዘብ ቀጣይ የርብርብ ማእከል መሆን እንደሚገባውም መግባባት ላይ ተደርሷል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.