Fana: At a Speed of Life!

ቦርዱ በተወሰኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ የተፈጸመው ጠቅላላ ጉባኤ እንዳያደርጉ መከልከልና ማሰር በወንጀል እንደሚያስጠይቅ አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 6 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰሞኑን አንዳንድ የፀጥታ አካላት በተወሰኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ የፈጸሙት ጠቅላላ ጉባኤ እንዳያደርጉ መከልከልና ማሰር በወንጀል እንደሚያስጠይቅ አስታወቀ፡፡

ቦርዱ በእናት እና በባልደራስ ፓርቲ ላይ ጠቅላላ ጉባኤ እንዳያካሂዱ በጎጎት ለጉራጌ አንድነትና ፍትህ ፓርቲ አስተባባሪዎች ደግሞ ከጉባኤ በኋላ መታሰራቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡

ፍትህ ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ የወንጀል ምርመራ መርቶ አጥፊዎች ላይ ክስ እንዲያቀርብ ቦርዱ ወስኗል፡፡

በኃይለኢየሱስ ስዩም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.