Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂን ፒንግ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሺ ጂን ፒንግ ለሶስተኛ ጊዜ የቻይና ፕሬዚዳንት ሆነው በመመረጣቸው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመልዕክታቸው÷ “ሺ ጂን ፒንግ በድጋሚ የቻይና ፕሬዚዳንት ሆነው በመመረጥዎ በራሴ፣ በኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ስም እንኳን ደስ ያለዎ” ብለዋል፡፡

በቀጣይም ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ያላትን ሀሉን አቀፍ ፣ ስተራቴጂክ ትብብር እና አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል፡፡
በዛሬው ዕለት በሙሉ ድምፅ የተመረጡት ከትናንት ጀምሮ በመካሄድ ላይ ባለው
14ኛው ብሔራዊ የሕዝብ ሸንጎ ሺ ጂንፒንግ የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት አድርጎ መምረጡ ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.