Fana: At a Speed of Life!

በሽግግር ፍትህ ላይ የሚያተኩር ጉባኤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፍትህ ሚኒስቴር ከአፍሪካ ህብረት ጋር በትብብር ያዘጋጀው በሽግግር ፍትህ ላይ የሚያተኩር ጉባዔ እየተካሄደ ነው።

በጉባዔው ላይ ዓለማቀፍ ባለሙያዎች ልምዳቸውን እንደሚያካፍሉ ተገልጿል።

የፍትህ ሚኒስትር ዴዔታ ዓለምአንተ አግደው በዚህ ወቅት ፥ መንግስት ለሽግግር ፍትህ መረጋገጥ ቁርጠኛ አቋም እንዳለው ገልጸዋል፡፡

አክለውም ፥ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥና ፍትህን ለማስከበር ያስችላልም ነው ያሉት።

ከዚህ ጋር ተያይዞም መንግስት ገለልተኛ የባለሙያዎች ቡድን ማቋቋሙንና ለተግባራዊነቱ እየሰራ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

ለውጤታማነቱና ለገለልተኛነቱም ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንደሚያደርግም ነው ያስታወቁት፡፡

በኢትዮጵያ የሚካሄደው የሽግግር ፍትህ ውጤታማ እንዲሆን የአፍሪካ ህብረት ሙሉ ድጋፍ አለው ያሉት ደግሞ የህብረቱ ተወካይ ፔሸንስ ቺራድዛ ናቸው።

በዚህም የሀገራትን ተሞክሮ ለኢትዮጵያ በሚስማማ መንገድ መተግበር ይገባልም ብለዋል፡፡

በአፈወርቅ እያዩ እና ታሪኩ ለገሰ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.