Fana: At a Speed of Life!

የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽነር በኢትዮጵያ ከጃፓን እና ስዊድን አምባሳደሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በኢትዮጵያ ከጃፓን እና ስዊድን አምባሳደሮች ጋር ተወያዩ፡፡

ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ÷ በኢትዮጵያ ለጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ በብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽኑ ስለ ተቋቋመበት ዓላማ፣ እስከ አሁን ስለተከናወኑ የዝግጅት ምዕራፍ ሥራዎች እና ከልማት አጋሮች ጋር በጋራ ስለሚሠሩ የትብብር ጉዳዮች ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አምባሳደር ኢቶ በበኩላቸው÷ ጃፓን የኢትዮጵያ ዋነኛ አጋር መሆኗን አስታውሰው ለኮሚሽኑ ሥራ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።

የስዊድን አምባሳደር ሀንስ ሄኒክም ÷ ስዊድን የሠላም ሥምምት ሂደቱን በቅርበት ስትከታተል እንደነበር እና የተሃድሶ ኮሚሽን ሥራዎቹንም ከግብ ለማድረስ የበኩሏን እንደምታደርግ አስታውቀዋል፡፡

ብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን ተጠሪነቱ ለሠላም ሚኒስቴር ሆኖ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 525/2015 ዓ/ም መቋቋሙ ይታወሳል ።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.