Fana: At a Speed of Life!

ሰሜን ኮሪያ በሣምንት ውስጥ ሦስተኛዋን ሚሳኤል ተኮሰች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሜን ኮሪያ አሁን ደግሞ አኅጉር አቋራጭ ባሊስቲክ ሚሳኤል መተኮሷ ተሠማ፡፡

ይህኛውን ጨምሮ በአንድ ሣምንት ጊዜ ውስጥ ሰሜን ኮሪያ ሚሳኤል ስትተኩስ ለ3ኛ ጊዜ መሆኑን አልጀዚራ አስታውሶ ዘግቧል፡፡

ዛሬ ደቡብ ኮሪያ ከባላንጣዋ የተወነጨፈባት ሚሳኤል ከዓመታት በኋላ ከጃፓን ጋር ጉባዔ በምትቀመጥበት ዕለት ነው፡፡

የኑክሌር አረር የመሸከም ዐቅም ያለው አኅጉር አቋራጭ ሚሳኤሉ ከፒዮንግያንግ ተተኩሶ 1 ሺህ ያኅል ኪሎ ሜትሮችን በማቋረጥ በኮሪያ ልሳነ ምድር እና ጃፓን መካከል ባለው ባሕር ማረፉ ተነግሯል፡፡

ሰሜን ኮሪያ ያስወነጨፈችው አኅጉር አቋራጭ ሚሳኤል እንዳይተኮስ ክልከላ የተጣለበት መሆኑን ደግሞ የደቡብ ኮሪያ ባለሥልጣናት ጠቁመዋልም ነው የተባለው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.