Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቀጣይ ጨዋታዎች በአዳማ ከተማ ይካሄዳሉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከ18ኛ ሳምንት ጀምሮ በአዳማ ከተማ እንደሚካሄድ ሊግ ካምፓኒው አስታውቋል፡፡

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አህጉራዊ ውድድር ምክንያት የተቋረጠው የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እስከ 17ኛ ሳምንት ድረስ በድሬዳዋ ከተማ ሲካሄድ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡

በቀጣይ ውድድሩ የሚካሄድበትን ከተማ ሲያመቻች የነበረው ሊግ ካምፓኒው÷ከ18ኛ ሳምንት ጀምሮ በአዳማ ከተማ እንደሚካሄድ አስታውቋል፡፡

በዚህ መሰረትም ተስተካካይ ጨዋታዎች እና የመጀመሪያዎቹ 5 የጨዋታ ሳምንታት በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሚካሄዱ ይሆናል፡፡

የሊጉ ቀጣይ አምስት ጨዋታዎች ደግሞ  በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ  ስታዲየም የሚከናወኑ መሆኑን ከቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.