Fana: At a Speed of Life!

በሞጆ ወደብና ተርሚናል የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያስችል የኬሚካል ርጭት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት በሞጆ ወደብና ተርሚናል ቅ/ጽ/ቤት የኮሮና ቫይረስን ወረርሽኝ ለመከላከል የሚያስችል የኬሚካል ርጭት ተካሄደ።

የሞጆ ወደብና ተርሚናል አብዛኛውን የአገራችንን የወጪና ገቢ ዕቃዎች የሚያስተናግድ እንደመሆኑ መጠን ድንበር አቋራጭ የከባድ ተሽከርካሪ ሹፌሮች፣ አስመጭና ላኪዎች፣የዕቃ አስተላላፊ ትራንዚተሮች፣ የድርጅቱ እና የሌሎች ተቋማት ሰራተኞች የሚገኙበት በመሆኑ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ የሞጆ ወደብና ተርሚናል ቅ/ጽ/ቤት ዳይሬክተር አቶ ደረጃ ሚደቅሳ ገልጸዋል።

በአሁኑ ሰዓትም በወደብና ተርሚናሉ ለሚገኙ ሰራተኞች ተከታታይነት ያለው የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት በመስጠት ላይ ይገኛል ተብሏል።

ማንኛውም ሰራተኛ ሆነ ደንበኛ ወደ ወደቡ ሲገባ የሰውነት ሙቀት ከመለካት ጀምሮ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች በማቅረብ ራሳቸውን ከበሽታው እንዲጠብቁ የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሆነ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ሰው የሚበዛባቸውን ዋና ዋና የወደቡ አካባቢዎች በመለየት የመግቢያ በርና ቁጥጥር፣ ቢሮዎች፣ መጋዘኖች፣ ካፌ እና ጋራዥ አካባቢ ያሉትን የጸረ ተህዋሲያን ኬሚካል ርጭት ተካሂዷል።

በተመሳሳይ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ድጋፍ በማድረግ በሞጆ ከተማ በሚገኙ ዋና ዋና መንገዶች የኬሚካል ርጭት እንደተደረገ አቶ ደረጀ ማስረዳታቸውን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.