Fana: At a Speed of Life!

በቂ የጤፍ እና ስንዴ ምርት አለ-ሚኒስቴሩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በቂ የጤፍ እና ስንዴ ምርት መኖሩን የንግድና ቀጠናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሰሞኑን በተከሰተው የጤፍ እና የስንዴ ዋጋ ንረት ላይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫው ÷በቂ ምርትና የምርት አቅርቦት ቢኖርም ኅገ-ወጥ ነጋዴዎች ከደላላ ጋር በመመሳጠር ገበያውን እንደፈለጉ እየዘወሩ መሆኑ ነው የተመላከተው፡፡

ወቅቱ ጤፍም ሆነ ስንዴ በሰፊው የተመረተበት መሆኑ ተመላክቶ በጥምረት አሻጥረኞችን በኅግ አግባብ ለመጠየቅ ስምምነት ላይ ተደርሷልም ነው የተባለው።

ከዛሬ ጀምሮ ከጤፍ ጋር ተያይዞ ምንም ዓይነት ኬላ እንዳይኖር ስለመደረጉም ተጠቁሟል።

ችግሩን ለመፍታት ምርት ከክልል በሥፋትና በጥራት ለማስገባት ስምምነት ላይ መደረሱም ተነግሯል።

በሸማች ማኅበራት እና በዕሁድ ገበያ በኩል ለህብረተሰቡ በሥፋት ተደራሽ ለመሆን ከመንግሥት ጋር መግባባት ላይ መደረሱም ነው የተገለጸው።

በመግለጫው ላይ የንግድና ቀጠናዊ ትሥሥር ሚኒስትር ዴኤታ ፣ የኦሮሚያ እና የአማራ ክልል አመራሮች እንዲሁም የኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ማኅበራት ምክትል ኮሚሽን ኮሚሽነር ተገኝተዋል።

በፈቲያ አብደላ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.