Fana: At a Speed of Life!

ጠፍቷል የተባለው የዩራኒየም ክምችት መገኘቱን ሊቢያ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠፍቷል የተባለው የዩራኒየም ክምችት መገኘቱን የሊቢያ ብሔራዊ ጦር ቃል አቀባይ ጀነራል ካሊድ ማህጁብ ገልፀዋል፡፡

ዩራኒየሙ የተገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኒውክሌር ኤጀንሲ መጥፋቱን ተከትሎ ማስጠንቀቂያ ከሰጠ ከአንድ ቀን በኋላ ነው፡፡

በሊቢያ ከመጋዘን ውስጥ ተሰርቋል የተባለው 2 ነጥብ 5 ቶን ዩራኒየም በሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል ዳርቻ ከቻድ ድንበር አቅራቢያ መገኘቱ ነው የተነገረው።

ጄኔራል ካሊድ ማህጁብ እንደተናገሩት የጠፉት እና የዩራኒየም ክምችት የያዙት 10 በርሜሎች የተገኙት ከማከማቻ መጋዘኑ 5 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ መሆኑን የአር ቲ ዘገባ አመላክቷል፡፡

ከጎረቤት ሀገር የመጡ አማፂያን ትላልቆቹ ሰማያዊ በርሜሎች መሳሪያ ወይም ጥይቶች ይዘዋል በሚል ከመጋዘኑ እንደሰረቋቸውና ኋላ ላይም ጥለዋቸው ሳይሄዱ እንዳልቀረ ጄነራሉ ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.