Fana: At a Speed of Life!

የፌደራል መንግስት ለሶማሌ ክልል የ15 ሚሊየን ብር የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ አበረከተ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 5 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል መንግስት ለሶማሌ ክልል የ15 ሚሊየን ብር የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ አበረከተ።

ድጋፉን የኢፌዴሪ ሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ እንዲሁም የገንዘብ ሚኒስቴር የፌደራል መንግስትን በመወከል አስረክበዋል።

የክልሉን መንግስት ወክለው ድጋፉን የተረከቡት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አደም ፋራህ ለተደረገው ድጋፍ በክልሉ ህዝብ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ድጋፉ የተለያዩ የእጅ ንጽህና መጠበቂያ ሳኒታይዘሮች፣ አልኮል፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎች፣ ፈሳሽ ሳሙናዎች፣ የሙቀት መለኪያ ኪቶችና ሌሎች ቁሳቁሶችን ያካተተ ነው።

ቁሳቁሱ ለበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች፣ ለአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚሽን፣ ለጤና ተቋማትና ለክልሉ አስተዳደር መከፋፈሉን ከሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የኢፌዴሪ የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስትር ወይዘሮ ፊልሰን አብዱላሂ የክልሉ አመራርና ሰራተኛ ከመንግስትና ከጤና ባለሙያዎች የሚሰጡ የጥንቃቄ ምክረ ሃሳቦችን በሚገባ መተግበርና ማስተግበር እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ሚኒስትሯ መጭውን የረመዳን ጾም በማስመልከት በፋፈም ዞን ባቢሌ ወረዳ ቁልጬ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ካምፕ በመገኘት ተፈናቃዮችን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ወቅት የተለያዩ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች አልባሳትና የማብሰያ ዕቃዎች ድጋፍ የተደረገ ሲሆን ሚኒስትሯም ከተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.