Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሕክምና ቁሳቁሶችን ለትግራይ ክልል አበረከተ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 5 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ለትግራይ ክልል አበረከተ።

ድጋፉ 30 ሺህ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል፣ 85 ሺህ የእጅ ጓንት እና 35 ሺህ ሊትር የንጽህና መጠበቂያ ሳኒታይዘርን ያካተተ ነው ተብሏል።

ቁሳቁሱን የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዮናስ አረጋይ ለትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ዛሬ አስረክበዋል።

አቶ ዮናስ ድጋፉ ቫይረሱን ለመከላከል ተጋግዘን መስራት እንዳለብን ማሳያ ነው ማለታቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.