Fana: At a Speed of Life!

የጤና ባለሙያዎች ብቃት ጥራት ላለው የጤና አገልግሎት ወሳኝ ነው- ዶ/ር ሊያ ታደሰ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ባለሙያዎች ብቃትና ተነሳሽነት ጥራት ላለው የጤና አገልግሎት ወሳኝ ነው ሲሉ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ተናገሩ፡፡

የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር 59ኛ ዓመታዊ ጉባኤ እና ዓለም አቀፍ የጤና አውደ ርዕይ እያካሄደ ነው።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር አንጋፋና ለጤናው ስርዓት በርካታ አስተዋጽዖ ማበርከቱን ተናግረዋል።

የጤና ሚኒስርቴርም በሀገር ደረጃ ያለውን የጤና ስርዓት ለማጎልበት የተለያዩ ስትራቴጂዎች ቀርጾ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራ ነው ብለዋል።

የጤና አገልግሎት ጥራትና ፍትሐዊነትን ለማረጋገጥ÷ መረጃን መሰረት ያደረገ የህክምና አገልግሎትን ለመስጠት፣ የአመራርና የጤና ፋይናንስ ስርዓትን ማጠናከር እንደሚገባም አንስተዋል፡፡

እንዲሁም የጤናው ዘርፍ ሰራተኞች ተነሳሽነት ያላቸው ብቁና ሙያዊ ሥነ ምግባር የተላበሱ እንዲሆኑ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር በዚህ ተግባር በቀደምትነት የተለያዩ ኮርሶችን በማዘጋጀት፣ ተደራሽነትን በማሻሻል፣ በአክሪዲተርነት እና በስልጠና አቅራቢነት እየሰራ ያለው ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

በመንግስትም ሆነ በግል ጤና ተቋማት የህክምና ቴክኖሎጂዎችን ማዘመን እንደሚገባና ለዚህም የሙያ ማህበራት፣ የህክምና ባለሙያዎች፣ የተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች እና የሚዲያው ተቋማት በተቀናጀ መንገድ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ሚኒስትሯ ጥሪ ማቅረባቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.