Fana: At a Speed of Life!

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የ90 ቀናት የሌማት ትሩፋት ተግባራትና ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ዣንጥራር አባይ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የ90 ቀናት የሌማት ትሩፋት ተግባራትና ሰው ተኮር ፕሮጀክትን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አደረጉ።

በክፍለ ከተማው ከ328 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የዶሮ እርባታ፣ የመብራት ዝርጋታ እና የተቀናጀ የከተማ ግብርና ስራ ፕሮጀክቶችን ጨምሮ 28 ፕሮጀክቶች መሰራታቸው ተገልጿል።

የተከናወኑት ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች የመልካም አስተዳደር እና የልማት ስራዎች ማሳያ መሆናቸውን የጠቀሱት የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አበራ ብሩ የ90 ቀናት ልማት የስራ ባህልን ለማሻሻል ተሞክሮ የተወሰደበት ነውም ብለዋል።

ምክትል ከንቲባ ዣንጥራር አባይ በበኩላቸው ከተማ አስተዳደሩ ዛሬ በተመረቁት ፕሮጀክቶች ጠቃሚ ስራዎችን በመስራቱ በርካቶችን ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚቻል አንስተዋል።

የተቀናጀ የከተማ ግብርና ስራውም ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ገልፀዋል።

ፕሮጀክቶቹን በማልማት በኩል ባለሀብቶች ተሳታፊ መሆናቸውም ተገልጿል።

በሜሮን ሙሉጌታ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.