Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት እና የጎንደር ከተማ ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከጀርመን አይ ኤች ኬ ሩትሊንገን ጋር በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት እና የጎንደር ከተማ ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት በጀርመን ከሚገኘው አይ ኤች ኬ ሩትሊንገን ጋር በጋራ ለመስራት ተስማሙ።

በጀርመን የተካሄደውን ስምምነት የተፈራረሙት የአማራ ክልል ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሰላሙ ደረጀ እና የአማራ ክልል ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ አሰፋ አላምረው ናቸው።

የአማራ ክልልና የጎንደር ከተማ ንግድ ምክር ቤቶች የቦርድ አባል የሆኑት አቶ አለልኝ ማስረሻ እንደገለፁት በቀጣይ ሶስት አመት በቱሪዝም እና በተለያዩ ዘርፎች ለነጋዴው እና ለንግድ ምክር ቤቱ የአቅም ግንባታ ለመስጠት እና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ለመስራት ተስማምተዋል።

ይህም የንግዱን ዘርፍ አቅም በማሳደግ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን እንደሚፈጥር ገልፀዋል።

በስምምነቱ ወቅትም የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ አቶ ጣሂር መሐመድ እና የሁለቱም ምክር ቤት ዋና ጸሐፊዎች በተጋባዥነት መገኘታቸውን አቶ አለልኝ ገልጸዋል።

በነቢዩ ዮሐንስ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.