Fana: At a Speed of Life!

በ ጅቡቲ ኢንተርናሽናል ሚት የአትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀናቸው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2015(ኤፍ ቢ ሲ) ለስድስተኛ ጊዜ በተካሄደው ‘ጅቡቲ ኢንተርናሽናል ሚት’ የአትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ ርቀቶች አሸንፈዋል፡፡

በ5 ሺህ ሜትር ሴቶች አለሽኝ ባወቀ 16 ደቂቃ ከ15 ሰከንድ ከ30 ማይክሮ ሰኮንድ በሆነ ሰዓት በቀዳሚነት አጠናቃለች።

እንዲሁም አዳኔ አንማው 16 ደቂቃ ከ18 ሰከንድ ከ66 ማይክሮ ሰከንድ ውድድሩን በሁለተኝነት ጨርሳለች።

በሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር በተካሄደ ውድድር አትሌት ነጻነት ደስታ 4 ደቂቃ ከ8 ሰከንድ ከ58 ማይክሮ ሰከንድ በቀዳሚነት አጠናቃለች።

ፍሬዘውድ ተስፋዬ 4 ደቂቃ ከዘጠኝ ሰከንድ ከ43 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ውድድሩን ሁለተኛ ሆና መጨረሷን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በወንዶች 1 ሺህ 500 ሜትር አትሌት አብዱልከሪም ተኬ 3 ደቂቃ ከ8 ሰከንድ ከ16 ማይክሮ ሰከንድ በቀዳሚነት አጠናቋል።

በተጨማሪም በወንዶች 800 ሜትር ኤፍሬም መኮንን ቀዳሚ ሆኖ ሲጨርስ በ5 ሺህ ሜትር ወንዶች ደግሞ አትሌት ዘነበ አየለ ሁለተኛ ወጥቷል።

በጅቡቲ ኢንተርናሽናል ሚት የአትሌቲክስ ውድድር ከኢትዮጵያ አትሌቶች በተጨማሪ የጅቡቲ፣ ሱዳን፣ ኡጋንዳ፣ ብሩንዲ፣ ሶማሊያ፣ ርዋንዳ፣ ኬንያ፣ ሴኔጋል እና ካሜሮን አትሌቶች ተሳትፈዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.