Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል የቤት ለቤት የኮሮና ቫይረስ ልየታ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 5 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የቤት ለቤት የኮሮና ቫይረስ ልየታ መጀመሩን አስታወቀ።

በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ፥ በክልሉ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት የቤት ለቤት የኮሮና ቫይረስ ልየታ መጀመሩን አስታውቀዋል።

በዚህም የሰውነት ሙቀት ልኬት በጤና ባለሙያዎች እንደሚደረግ መናገራቸውን ከኦሮሚያ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ህብረተሰቡ በዚህ ስራ ላይ ለተሰማሩ የጤና ባለሙያዎች አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.