Fana: At a Speed of Life!

በኮንሶ ዞን ከ227 ሺህ በላይ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል ተባለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ኮንሶ ዞን በተከሰተው ድርቅ ከ227 ሺህ በላይ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተመለከተ።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዳዊት ገበየሁ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት ÷ ባለፉት አራት ዓመታት በዞኑ የዝናብ እጥረት እና የሥርጭት መዛባት በመከሰቱ በዞኑ በአራት ወረዳዎች ድርቅ ተከስቷል፡፡

ለአብነትም በኬና ወረዳ የሚገኙ ዜጎች የምግብ እና ውሃ እጥረት እንዳጋጠማቸው ጠቁመው÷ ከ65 ሺህ በላይ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

ላለፉት አራት ዓመታት ምርት ማምረት ስላልተቻለ ለከፍተኛ የምግብ እጥረት መጋለጣቸውን እና እየቀረበ ያለው ድጋፍም አነስተኛ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ከታኅሣሥ ወር ወዲህ እርዳታ እንዳልቀረበላቸው እና በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ስለመሆናቸው አስረድተዋል፡፡

በየጊዜው የተረጂዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ጠቅሰው÷ ድጋፉን በጊዜ ማቅረብ አለመቻሉን ተናግረዋል፡፡

እዲሁም ድርቁን ሽሽት ተማሪዎችን ጨምሮ ወጣቶች ወደ ሌላ አካባቢ እየተፈናቀሉ ነው ያሉት አቶ ዳዊት÷ እናቶች እና ሕጻናትም ለከፋ የጤና እክል እየተዳረጉ ነው ብለዋል፡፡

ሰሞኑን እየጣለ ያለው ዝናብ ተስፋ ሰጪመሆኑን አመላክተው እስከ ሰኔ ድረስ ተጉጂዎች እርዳታ እንደሚስፈልጋቸው አስገንዝበዋል፡፡

ድርቁ በሰው እና በእንሰሳት ላይ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።

በመራኦል ከድር እና ሰዓዳ ጌታቸው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.