Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ እናትና ልጆችን ጨምሮ አራት ሰዎች በጎርፍ ተወሰዱ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ትናንት ምሽት በጣለው ዝናብ እናት እና ልጆችን ጨምሮ አራት ሰዎች በጎርፍ መወሰዳቸው ተሰምቷል፡፡

ትናንት ምሽት የጣለውን ዝናብ ተከትሎ ከምሽቱ 12:05 ሰዓት በንፋስስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ማንጎ ሰፈር ወንዝ ዳርቻ ላይ በሚገኙ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ጎርፍ ገብቶ እንደነበር ተገልጿል፡፡

በዚህም እናትና ልጆችን ጨምሮ አራት ሰዎች በጎርፍ ተወስደዋል።

የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን እንዳስታወቀው፥ በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ የነበሩ የ3፣ የ13፣ የ15 እና የ46 ዓመት ሴት ናቸው በጎርፉ የተወሰዱት።

የ46 ዓመቷ ሴት በጎርፍ የተወሰዱት የ13 እና የ15 ታዳጊዎች ወላጅ እናት መሆናቸውን በኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የዋናተኛ ቡድን ባደረገው ፍለጋ የአራቱንም አስከሬን አግኝቷል ብለዋል።

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia #Flood #AddisAbaba

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.