Fana: At a Speed of Life!

የአእምሮ እድገት ውስንነት ላለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እድል መስጠት ይገባል -ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአእምሮ እድገት ውስንነት ላለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እድል መስጠት ይገባል ሲሉ የኢፌዲሪ ፕሬዚደንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ፡፡

ዓለም አቀፉ የአእምሮ እድገት ውስንነት (የዳውን ሲንድረም) ቀን “ስለ እኛ ከኛ ጋር” በሚል መሪ ሃሳብ በዲቦራ ፋውንዴሽን አዘጋጅነት በወዳጅነት ፓርክ እየተካሄደ ነው።

በመርሐግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት ፕሬዚደንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ  ÷ የአእምሮ እድገት ውስንነት የተዘነጋ ፤ ነገር ግን ልዩ ትኩረት የሚፈልግ ነው ብለዋል።

ህብረተሰቡ ይህንን ችግር በመረዳትም ለእነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች እድል መስጠት እንደሚባ ጠቁመው ፥ ቀኑ ከአንድ ቀን ባለፈ ዓመቱን ሙሉ ሊሰራበት የሚገባ መሆኑን አመላክተዋል።

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው ፥ የአእምሮ እድገት ውስንነት ውስጥ ላሉ  ዜጎች የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት በሚኒስቴሩ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቁመዋል።

የዲቦራ ፋውንዴሽን መስራች አቶ አባዱላ ገመዳ ÷የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ዜጎች እንደማንኛውም ዜጋ ሀገራቸውን የሚጠቅሙ ናቸው  ብለዋል፡፡

ፋውንዴሽኑ ሀገራቸውን የሚያኮሩ ትውልድን መፍጠር ዓላማ አድርጎ በዚህ ችግር ውስጥ ያሉ ዜጎችን እያገዘ ይገኛል ማለታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.