በሶል ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀናቸው
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኮሪያ በተካሄደው የ77ኛው ሶል ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡
በውድድሩ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ ርቀቱን አጠናቀዋል፡፡
በውድድሩ አትሌት አምደወርቅ ዋለልኝ 2 ሰዓት ከ5 ደቂቃ ከ26 ሴኮንድ በመግባት ቀዳሚ ሲሆን ፥ አትሌት ሺፈራው ታምሩ እና አትሌት ሀፍቱ አሰፋ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል፡፡
ባለፈው ዓመት በተካሄደው 76ኛው የሶል የወንዶች ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ሞስነት ገረመው አሸናፊ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡