Fana: At a Speed of Life!

የሀገሪቱን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ የወጣቶች ሚና ከፍተኛ ነው – አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገሪቱን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ የወጣቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ተናገሩ፡፡

“የብልጽግና ፓርቲ መሰረታዊ አስተሳሰቦችና እሳቤዎች” በሚል ርዕስ ከመጋቢት 3 እስከ 11 ቀን 2015 ዓ.ም ለብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቋል፡፡

በዚህ ወቅት የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ ÷ወጣቶች የፓርቲውን መሰረታዊ እሳቤዎች በመረዳት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት መስራት አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ለመናድ በርካቶች የተሳሳቱ አጀንዳዎች ላይ በማተኮር እኩይ አላማቸውን ለማስፈጸም እየሰሩ መሆኑን የተናገሩት አቶ አደም ወጣቶች ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከርና ዘላቂ ሰላምን ለመገንባት መስራት አለባቸውም ብለዋል።

የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪል ማህበራት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መለሰ ዓለሙ÷ ብልጽግና የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ለመሆን እየሰራ ያለ ፓርቲ መሆኑን ጠቅሰ ወጣቶች አገርን ከድህነት ወደ ብልጽግና የማሻገርና በመደመር እሳቤ አገራዊ አንድነትን ላይ ሊሰሩ ይገባል ነው ያሉት፡፡

የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ጌታቸው ጀምበር በበኩላቸው÷ ወጣቶች አገሪቱ የጀመረችውን ልማትና ብልጽግና እንዲረጋገጥ፤የፓርቲው መርሆዎች ተጠብቀው ተግባራዊ እንዲሆኑ መስራት አለባቸው ማለታቸውን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.