Fana: At a Speed of Life!

ዋልያዎቹ በአቋም መለኪያ ጨዋታ ሩዋንዳን 1ለ0 አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ባደረገው የአቋም መለኪያ ጨዋታ ሩዋንዳን 1ለ0 አሸንፏል፡፡

ብሄራዊ ቡድኑ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ከጊኒ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ የአቋም መለኪያ ጨዋታውን ከሩዋንዳ ጋር ዛሬ 10 ሰዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም አካሂዷል፡፡

በጨዋታውም ዋልያዎቹ 1ለ0 አሸንፈዋል፡፡

ግቡን ከነዓን ማርክነህ በ83ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።

በኮትዲቭዋር አስተናጋጅነት እ.አ.አ በ2023 በሚካሄደው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ ከጊኒ ጋር በሞሮኮ ራባት መጋቢት 15 እና 18 ቀን 2015 ዓ.ም ጨዋታዋን ታደርጋለች።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.