Fana: At a Speed of Life!

ኢንጂነር ታከለ ኡማ የተቋቋሙ የምግብ ባንኮችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በአዲስ አበባ የተቋቋሙትን የምግብ ባንኮች ጎበኙ።

ወደ ምግብ ባንኮቹ የተለያዩ የምግብ አይነቶች እየገቡ ሲሆን ማህበረሰቡ ድረስ የሚደርስ መዋቅርም ተዘርግቷል።

የምግብ ባንኮቹ ከኮሮና ቫይረስ መከሰት ጋር በተያያዘ የምግብ ችግር የሚገጥማቸውን ዜጎች ለመደገፍ የተቋቋሙ ሲሆን የከተማዋ ነዋሪዎችም ድጋፍ እያደረጉ ይገኛል።

ኢንጂነር ታከለ ኡማ ወቅቱ መረዳዳትንና ያለንን ማካፈልን የሚጠይቅ እንደመሆኑ ነዋሪዎች የተቻላቸውን ድጋፍ ወደ ምግብ ባንኮቹ እንዲያስገቡ ጥሪ ማቅረባቸውን ከአዲስ አበባ ከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.