Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያን እና የመንን ታሪካዊ ግንኙነት የሀገራቱን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በመጠቀም ማደስ ያስፈልጋል – አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 11 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን እና የመንን ታሪካዊ ግንኙነት ለማደስ ዘመናትን ያስቆጠረውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከየመኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ አዋድ ጋር  ተወያይተዋል።

በውይይታቸው ወቅትም  ኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለሚኒስትሩ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ከዚህ ባለፈም የሀገራቱን ታሪካዊ ግንኙነት በጥቅም ብቻ ሳይሆን ዘመናትን ያስቆጠረውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን በአግባቡ በመጠቀም ማደስ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.