Fana: At a Speed of Life!

ዋሊያዎቹ ከጊኒ ጋር ለሚያደርጉት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ወደ ሞሮኮ አቀኑ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ከጊኒ አቻው ጋር ለሚያደርገው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ወደ ሞሮኮ አቀና፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን በኮትዲቯር አስተናጋጅነት በሚካሄደው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ ከጊኒ ብሔራዊ ቡድን ጋር የምድብ ማጣሪያ ጨዋታውን መጋቢት 15 እና 18 ቀን 2015 ዓ.ም በሞሮኮ ያደርጋል።

የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ በማድረግ ከመጋቢት 6 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ልምምዳቸውን ሲያደርጉ ቆይተዋል።

ዋልያዎቹ ከትናንት በስቲያ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከሩዋንዳ አቻቸው ጋር ባደረጉት የአቋም መለኪያ ጨዋታ በከነዓን ማርክነህ ግብ 1 ለ 0 ማሸነፋቸው ይታወቃል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በምድብ አራት ከግብጽ፣ ከማላዊና ከጊኒ ጋር ተደልድሏል፡፡

እስከአሁን ባደረጋቸው ሁለት ጨዋታዎችም በሦስት ነጥብ እና በአንድ የግብ ክፍያ ምድቡን እየመራ እንደሚገኝ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

#Ethiopia #waliawochu #ethiopiannationalfootballteam #africafootball

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.