Fana: At a Speed of Life!

ሲዳማ ክልል ባለፉት 6 ወራት ከ3 ሚሊየን በላይ ጎብኚዎችን አስተናገደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 6 ወራት ከ3 ሚሊየን በላይ የሀገር ዉስጥና የዉጭ ጎብኚዎች በሲዳማ ክልል ጉብኝት ማድረጋቸውን የክልሉ መንግስት ገልጿል።

እየተካሄደ ባለዉ የክልሉ ምክር ቤት 6ኛ ዙር 2ኛ የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ነዉ በእነዚህ ወራት ዉስጥ ከ3ሚሊየን በላይ ጎብኚዎች ክልሉን መጎብኘታቸዉ የተገለፀው።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ፥ በ6 ወራት ዉስጥ ከ36 ሺህ በላይ የዉጭ ሀገር ጎብኚዎች ክልሉን እንዲጎበኙ ታቅዶ የነበረ ሲሆን ÷ 25 ሺህ 773 ጎብኚዎች ክልሉን ጎብኝተዉ መመለሳቸውን ገልፀዋል።

ከዚህም ባሻገር 2 ነጥብ 7 ሚሊየን የሀገር ዉስጥ ጎብኚዎች ክልሉን እንዲጎበኙ ታቅዶ በተሰራዉ ስራ 3 ነጥብ 75 ሚሊየን የሀገር ዉስጥ ጎብኚዎች ክልሉን እንዲጎበኙ ማድረግ መቻሉን ነዉ የተናገሩት።

ከዉጭ እና ከሀገር ዉስጥ ጎብኚዎችም 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ ከ2 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉን ጠቅሰዋል።

በቢቂላ ቱፋ እና ታመነ አረጋ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.