Fana: At a Speed of Life!

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የተፈቀደ ካፒታሉ ወደ 221 ቢሊየን ብር ከፍ እንዲል ወሰነ

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት÷የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን በግንባታ ላይ ያሉ መሰረተ ልማቶች እንዲጠናቀቁና የተጠናቀቁት ወደ ስራ እንዲቡ የተፈቀደ ካፒታሉ ወደ 221 ቢሊየን ብረ ከፍ እንዲል ወሰነ፡፡

ሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው18ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ምክር ቤቱ ተወያይቶ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

 
ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው በመንግሥት ባለቤትነት የተያዙ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡
 
የቀረበው ረቂቅ አዋጅም የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የኮርፖሬት አስተዳር ሥርዓት ግልፅነትን እና ተያቂነትን የሚያረጋግጥ እንዲሆን፣ የኮርፖሬት ፋይናንስ አስተዳደር ሥርዓታቸውን በማዘመን ተወዳዳሪነታቸውን እና ውጤታማነታቸውን ማጠናከር የሚገባ በመሆኑ፣ ትርፋማነታቸውን በማይጎዳ መልኩ የማህበራዊ አገልግሎት ግዴታቸውን በውጤታማነት መወጣት እንዲችሉ የልማት ድርጅቶች ያለባቸውን የዕዳ ጫና ማሻሻል የሚያስችል በመሆኑ በአጠቃላይ በአገር ኢኮኖሚ እድገት ላይ የጎላ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡
 
ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል እንዲጸድቅ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
 
በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው ኢትዮጵያ ከሉግዘምበርግ መንግስት እንዲሁም ከስዊዝ ኮንፌዴሬሽን ጋር ተደራራቢ ግብርን ለማስቀረት እና የታክስ ማጭበርበርን ለመከላከል ያደረገቻቸውን ስምምነቶችን ለማጽደቅ በቀረቡ ረቂቅ አዋጆች ላይ ነው፡፡
 
ኢትዮጵያ ከሁለቱ መንግስታት ጋር ተደራራቢ ግብን ለማስቀረት እና የታክስ ማጭበርበርን ለመከላከል ያደረገቻቸው ስምምነቶች የሁለቱ ሀገራት ባለሃብቶች ሃብታቸውን በአገራችን ኢንቨስት እንዲያደርጉ በማበረታታት ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያለው ከሆኑም በላይ ባለሃብቶቹ ለአንድ ገቢ ከአንድ ጊዜ በላይ ግብር እንዳይከፍሉ የሚያደርግ በሆኑ ስምምነቶቹን ለማስጸደቅ ረቂቅ አዋጆችተዘጋጅተው ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርበዋል፡፡
 
ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጆቹ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብዓችን በማከል እንዲጸድቁ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
 
በጨረሻም ምክር ቤቱ የተወያየው የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ማቋቋሚያ ደንብ ለማሻሻል በቀረበ ረቂቅ ደንበ ላይ ነው፡፡
 
የኮፖሬሽኑን የተፈቀደ እና የተከፈለ ካፒታል በማሻሻል የተቋቋመበትን ዓላማና ተልዕኮ ለማሳካት እንዲችል በተለይም በግንባታ ላይ ያሉ የባቡር መሰረተ ልማቶች እንዲጠናቀቁ ፣የተጠናቀቁትም ወደ ስራ እንዲቡ፤ በቀጣይ ለሚገነቡ የባቡር መረተልማቶች የተሻለ አቅም እንዲኖረው የተፈቀደ ካፒታሉ ወደ ብር 221 ቢሊየን ከፍ እንዲል በጥሬ ገንዘብና በአይነት የተከፈለ ካፒታሉ ደግሞ ብር 120 ቢሊየን እንዲሆን ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡
 
ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቡ ላይ ተወያይቶ ግብዓቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲው በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.