Fana: At a Speed of Life!

ሰሞኑን በሞግዚቷ የተሰረቀችው የ2 ዓመት ሕጻን በሱሉልታ መገኘቷን ፖሊስ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከቀናት በፊት በሞግዚቷ ተሰርቃ የተወሰደችው የ2 ዓመቷ ሕጻን ሶሊያና ዳንኤል ከብሄራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ጋር በመተባበር በተደረገ ክትትል በሱሉልታ ክፍለ ከተማ መገኘቷን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ሕጻን ሶሊያና ሳሪስ አዲስ ሰፈር ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ሐሙስ መጋቢት 7 ቀን 2015 ዓ.ም ረፋድ ላይ ቤዛ በቀለ በተባለችው የቤት ሰራተኛቸው ተሰርቃ ስለመወሰዷ በተለያዩ ማሕበራዊ ትስስር ገፆች መረጃው ሲሰራጭ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ በሕጻኗ ወላጆች የቀረበለትን አቤቱታ ተቀብሎ ከብሄራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ጋር በመቀናጀትና ወደተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞችና አካባቢዎች በመሄድ ጭምር አስፈላጊ መረጃዎችን በማሰባሰብ ክትትል ሲያደርግ መቆየቱን ገልጿል፡፡

በዚህም ቤዛ በቀለ ዛሬ ሱሉልታ ክፍለ ከተማ ወሰርቢ ወረዳ በአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ ሕጻን ሶሊያና ዳንኤልን ደብቃ በተቀመጠችበት በቁጥጥር ስር መዋሏን ነው ፖሊስ ያሳወቀው፡፡

ተጠርጣሪዋ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋለች በኋላ፥ 40 ሺህ ብር ይከፈልሻል ብለው ሰዎች ስላግባቧት ህፃኗን ሰርቃ መሰወሯን ተናራለች፡፡

በወንጀሉ ላይ ተሳትፎ አላቸው የተባሉ ሌሎች ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ምርመራው መቀጠሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ገልጿል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.