Fana: At a Speed of Life!

አፈ ጉባዔ  አገኘሁ ተሻገር ከየመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ከየመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ አዋዳህ ቢን ሙባረክ ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይቱ  አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር÷በሁለቱ ሀገራት መካከል ዘመናትን ያስቆጠረ ዘርፈ ብዙ ግንኙነቶች እንደነበሩ ጠቅሰው በቀጣይም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሻገር ስራዎች እንደሚሰሩ አመላክተዋል፡፡

የየመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር አሕመድ አዋዳህ በበኩላቸው÷ በየመን በሺህዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ የስራ መስኮች ተሰማርተው እየሠሩ እንደሚኖሩ ገልጸዋል፡፡

ዜጎችን ወደ አገራቸው ለመመለስ የተጀመረውን ጥረት መንግስታቸው እንደሚያግዝ አረጋግጠዋል።

እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግስት በተለይ በአፍሪካ ቀንድ የሚስተዋለውን ሽብርተኝነት ለመከላከል ያላውን ጽኑ ፍላጎትና ተነሳሽነት መንግስታቸው እንደሚደግፍና ለዚህም አድናቆት እንዳለው መግለጻቸውን ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.